
ይሳተፉ
አባል ይሁኑ
የዝክረ ነዳያን ቤተሰብን በመቀላቀል የለውጥ ዓጋር ይሁኑ። በቌሚ አባልነት የሚያደርጉት ድጋፍ፣ በተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ህይወት ላይ ተጨባጭ ለዉጥ ያመጣል።
የወገናችንን ዘርፈ ብዙ ችግር ፤ ከሀገሩ ሰዉ በላይ ማን አዉቆት ማን ጠይቆት ማን ተረድቶት ማንስ ደግፎት። የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ እንዲል፤ የኢትዮጵያውያን ችግር በኢትዮጵያውያን እፈታዋለዉ ቡሎ እየሰራ ያለዉን ዝክረ ነዳያንን በመቀላቀል ለወገኖ ዓለኝታ በመሆን ከወገን ጎን በመቆም ብቻዉን ተዘንግቶ ያለአስታዋሽ እንዳልቀረ በዓባልነቶ ያረጋግጡለት።
ስፖንሰር ይሁኑ
ለተፈናቀሉ ወገኖ በፍጥነት በመድረስ እና መልሶ በማቌቌም ዘላቂ ለዉጥ በወገኖ ሕይወት ላይ ለመፍጠር ዝክረ ነዳያንን በስፖንሰርነት ይደግፉ።
ግለሰቦችን ፣ ፕሮጀክቶችን እና ፕሮግራሞችን ስፖንሰር የሚያደርጉበትን የተቀላጠፈ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የሰራ ሂደት ዝክረ ነዳያን ያመቻቸ ሲሆን ይህን በመቀላቀል በወገኖ ሕይወት ላይ ዘላቂ ተፅዕኖ ይፍጠሩ።
በመዋጮ ይሳተፉ
የሚያደርጉት ድጋፍ ህይወትን የመለወጥ እና ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ተስፋን ለማምጣት የሚያስችል ሃይል አለው። ለዝክረ ነዳያን በመለገስ፣ የመልሶ ማቋቋም እና ዘላቂ ተጽእኖ ለመፍጠር የተልዕኳችን ወሳኝ አካል ይሆናሉ። ማንኛውም አስተዋፅዖ፣ መጠኑ ምንም ይሁን ምን፣ የርህራሄ እና የመተሳሰብ መገለጫ ከመሆኑም ባሻገር የወገንዋን ህይወት በተግባር የሚቀይር ነው።
ዛሬ ይለግሱ እና ድጋፍዎ በጣም በሚያስፈልጋቸው ወገንዋ ህይወት ውስጥ ሊያመጣ የሚችለውን የማይታመን ለውጥ ይመስክሩ።
በበጎ ፈቃደኝነት ይሳተፉ
ዝክረ ነዳያን ያነገበዉ ዓላማ በገንዘብ ብቻ ሊፈታ እንደማይችል ጠንቅቆ ይረዳል። ስለሆነም ከገንዘብ ባሻገር ጊዜዋን በበጎ ፍቃደኝነት በድርጅቱ በርካታ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ሙያዊ ድጋፎን እንዲያበረክቱ ወገናዊ ጥሪዉን ያቀርባል።
ድርጅታዊ ድጋፍ
በኮርፖሬት ስፖንሰርነት በመሳተፍ በጋራ ዓላማ ላይ ከእኛ ጋር በመስራት የኢትዮጵያውያን ህይወት በጋራ መቀየር እንችል ዘንድ የዝክረ ነዳያን አጋር በመሆን ድርጅታዊ ማህበራዊ ሃላፊነትዋን ይወጡ።
