ፕሮጀክቶች
የማዳን ስራዎች
በምናደርገው የማዳን ስራ በሰው እና በተፈጥሮ ምክንያት ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን የእርዳታ እጃችንን ለመዘርጋት አላማ አለን። ድርጅታችን አደጋ የተጋረጠባቸዉ ወገኖቻችንን ላይ ትኩረት በማድረግ በአፋጣኝ የሚታደጉበትን መንገድ ለማረጋገጥ ያለመታከት ይሰራል፣ ይህም በችግር ጊዜ የተስፋ ብርሃን ይፈጥራል።ከሀገር ውስጥ ድርጅቶች እና የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ማንም ወገን በችግሩ ጊዜ የማይዘነጋበት ኢትዩጵያን ለመፍጠር እንጥራለን።
1
2
ሰብአዊ እርዳታ
የእኛ የሰብአዊ እርዳታ ተነሳሽነቶች ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ተገቢዉን ድጋፎ በማቅረብ ጽናትን በማጎልበት የወገናችንን ክብር ወደነበረበት መመለስ ላይ ያተኩራል። አስፈላጊ አቅርቦቶችን ከማቅረብ ጀምሮ የጤና እና የንፅህና አጠባበቅ ፕሮግራሞችን ተግባራ ዊ በማድረግ፣ ህይወትን ከፍ ለማድረግ እና ወገናችንን ለማብቃት እንተጋለን።
3
የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራሞች
በታለመላቸው የመልሶ ማቋቋም መርሃ ግብሮች፣ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን መልሰው እንዲገነቡ እና ህልማቸዉን እንዲያሳኩ እንረዳለን። የምክር፣ የሙያ ስልጠና እና የማህበረሰብ ውህደት አገልግሎቶችን በመስጠት፣ ወገኖቻችንን መልሶ በማቋቋም የወደፊት ተስፋው ብሩህ እንዲሆን ያለመታከት እንሰራለን።
4
የማህበረሰብ ተደራሽነት ፕሮግራሞች
የማህበረሰብ ተደራሽነት ፕሮግራሞች በአካባቢ ማህበረሰቦች መካከል አንድነትን እና ትብብር በማጎልበት ላይ ያተኩራል። በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ፣ ከሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እና ግንዛቤን በማሳደግ እና ጠንካራ የድጋፍ አውታር በመፍጠር እና በመገንባት የተደራሽነት አላማ ግብ ያደርጋል።